የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ፡ የቆንስላ አገልግሎት መጀመር አስመልክቶ የተዘጋጀ ማስታወሻ
በእንግሊዝ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭት አስመልክቶ የታዩ ለውጦችን ከግምት በማስገባት ኤምባሲያችን አገልግሎቱን አስመልክቶ ያስቀመጣቸውን የጥንቃቄ እርምጃዎች ለተገልጋዮች ማሳወቅ አስፈልጓል።
በዚህ ወቅት የጤና እና ደህንነት የሁሉም ሰው ጉዳይ እና ቅድሚያ ተሰጥቶት ሊታሰብበት የሚገባ መሆኑ ታምኖበት፣ኤምባሲው የእለት ከእለት ስራዎችን በሚያከናውንበት ወቅት የተገልጋዮችን እና የሰራተኞችን ደህንነት ቅድሚያ ሰጥቶየሚሰራ ይሆናል።
የስራ ቦታ አካባቢ ደህንነት ለማስጠበቅ እና ቅድመ መከላከልን በማጠናከር የማህበረሰብ ጤና ሳይንስ መመሪያን መሰረት በማድረግ የጥንቃቄ እርምጃዎች እየተወሰዱ ይገኛሉ። በዚህም መሰረት ኤምባሲያችን የሚከተለውን የስራ ጊዜ ሰሌዳ እና መመሪያ አውጥቷል።
የቆንስላ አገልግሎት የስራ ሰዓት
ከሰኞ እስከ አርብ
ጊዜ፡ ከ10.00 am – 4.00 pm
እ.ኤ.አ ጁን 08/2020 ጀምሮ የኤምባሲያችን ቆንስላ ክፍል ለተገልጋዮች ክፍት እንደሚሆን በማሳወቅ የሚከተሉትን አገልግሎቶች በቀጠሮ ብቻ የሚያስተናግድ ይሆናል።
- ቪዛን በተመለከተ የዲፕሎማቲክ እና ሰርቪስ ቪዛ አገልግሎት ብቻ የሚሰጥ ይሆናል። በሌላ ማስታወቂያ እስከሚገለፅ ድረስ ሌሎች መደበኛ የቪዛ ጥያቄዎች ለሚፈልጉ ደንበኞች በተከታዩ ድረ-ገፅ በመግባት ማመልከት ይቻላል https://www.evisa.gov.et ወይም በአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የመዳረሻ(On arrival) ቪዛ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- አዲስ የመታወቂያ ካርድ ማመልከቻዎች (ዘወትር ሰኞ እና አርብ)
- አዲስ የፓስፖርት ማመልከቻዎች (ዘወትር ረቡዕ እና አርብ)
- ሌሴፓሴ እና ሌሎች የጉዞ ሰነዶች (ዘወትር ረቡዕ እና አርብ)
- የውክልና ሰነዶች (ዘወትር ማክሰኞ እና ሃሙስ) የሚስተናገዱ ይሆናል
በሌላ ማስታወቂያ እስኪገለፅ ድረስም የሚከተሉትን አገልግሎቶች በፖስታ ብቻ የምናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን።
- ፓስፖርት እድሳት
- የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ እድሳት እና
- የሰነድ ማረጋገጥ አገልግሎቶች
በፖስታ እንዴት ማመልከት እንደሚገባ የእያንዳንዱን አገልግሎት ዝርዝር ጉዳይ በሚከተለው ድረ-ገፅ መመልከት ይቻላል www.ethioembassy.org.uk/consular-services
ለድንገተኛ ጉዳዮች በሚከተለው ስልክ ቁጥር በመደወል ምላሽ የሚሰጥ መሆኑን 0207 838 3898 ወይም በተከታዩኢሜይል መልዕክት ማድረስ ይቻላል ca@ethioembassy.org.uk። ለድንገተኛ ቀጠሮዎች የእያንዳንዱን ጉዳይ ምንነት መሰረት በማድረግ የሚከናወን ይሆናል።
ተጨማሪ አዳዲስ አሰራሮችና ተለዋጭ መመሪያዎች ሲኖሮ የሚገለፅ ይሆናል።
ለኤምባሲ ጎብኝዎች
በእንግሊዝ መንግስት ወቅታዊ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የCOVID-19 ስርጭት አሁንም ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልገው በተደጋጋሚ ተጠቅሷል። ስለሆነም ለተገልጋዩና ላገልጋዩ ጤንነት ሲባል ቫይረሱን ለመከላከል የሚያስችሉ ጥንቃቄዎች ተግባራዊ እንዲደረጉ ምክራችንን እንቀጥላለን። በመሆኑም፡-
- ማንኛውም አገልግሎት ፈላጊ ኤምባሲ ከመምጣቱ በፊት በተከታዩ ስልክ ቁጥር በመደወል ቀድሞ የቀጠሮ ጊዜ ሰሌዳ ማስያዝ ይጠበቅበታል ►0207 838 3877።
- የህመም ስሜት ያለበት፣ የኮቪድ-19 ምልክቶች ያሉበት፣ ወይም ደግሞ በቅርቡ ቫይረሱ በከፍተኛ ሁኔታ ካጠቃቸው አገሮች የመጣ እና ወደ ኤምባሲያችን ጉብኝት ማድረግ ለሚፈልግ ማንኛውም ደንበኛ/አገልግሎት ፈላጊ ከ14 ቀናት በኋላ ብቻ ለአገልግሎት መምጣት እንደሚገባ ግንዛቤ መውሰድ ያስፈልጋል። ይህ መልዕክት ከታመመ ሰውጋር ወይም ከኮቪድ-19 በሽተኛ ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎችም ያጠቃልላል።
- ወደ ኤምባሲ የሚመጣ ማንኛውም ደንበኛ/ተገልጋይ የፊት መሸፈኛ ወይም ጭምብል መልበስ ይጠበቅበታል።
- ወደ ኤምባሲው ቅጥር ግቢ ከመግባት እና ከሰራተኞች ጋር ከመገናኘት በፊት እጅ መታጠብ/ሳኒታይዘር መጠቀም ያስፈልጋል።
- ማንኛውም ጎብኝ/አገልግሎት ፈላጊ ኤምባሲ ግቢ ውስጥ ከሌሎች ሰዎች (የቤተሰብ አባላት ያልሆኑ) ጋር ቢያንስ የ2 ሜትር ርቀት በመጠበቅ መገልገል ይገባል።
- በኤምባሲ ውስጥ የሚገኙ ቅፆች ሲሞሉ የራሶትን ብዕር ወይም እስክብሪቶ እንዲጠቀሙ ይመከራል።
ወደ ኢትዮጵያ የሚደረግ ጉዞ
እ.ኤ.አ አርብ፣ ማርች 13 /2020 ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የኮቪድ-19 ታማሚ ማግኘቷን ያሳወቀች ሲሆን በዛሬው እለት ማለትም እ.ኤ.አ ጁን 05/2020፣ አጠቃላይ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1805 ደርሷል።
የኮቪድ-19 ወረርሺኝ ከተከሰተ ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግስት የቫይረሱን መስፋፋት ለመከላከል የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል። የመንግስት የኮቪድ-19 መከላከያ እና ጥንቃቄ መመሪያ በተከታዩ ሊንክ ያገኙታል: www.ethioembassy.org.uk/travel-advisory
እ.ኤ.አ ከማርች 23/2020 ጀምሮ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ማንኛውም ተጓዥ መንግስት ባዘጋጃቸው የለይቶ ማቆያ ሆቴሎች እና ቦታዎች ለ14 ቀናት እራሳቸውን ለይተው እንዲያቆዩ እየተደረገ ይገኛል። ዲፕሎማቶች በራሳቸው ኤምባሲ ውስጥ ለ14 ቀናት እራሳቸውን ለይተው እንዲያቆዩ ይጠበቃል።
የ14 ቀን ለይቶ ማቆያ የተላላፊ (Transit) ተጓዦችን አይመለከትም። የTransit ተጓዦች ወደሌላ መዳረሻ የሚሄዱበት አየር መንገድ እስኪሳፈሩ ድረስ በስካይላይት ሆቴል እንዲቆዩ ይደረጋል።
Latest News
Browse allwe appreciate your help.