Back To Your Origins
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ኤምባሲ ለንደን የሚሸፍናቸው ሀገራት ነዋሪ ለሆናችሁ ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የቀረበ ታላቅ ሀገራዊ ጥሪ!
ክቡር የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ሁለተኛው ትውልድ የኢትዮጵያ ዳያስፖራዎች በሦስት ዙር ወደ ሀገራቸው በመግባት ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ እና የባህል መሠረታቸውን እንዲያውቁ የቀረበውን ጥሪ በመቀበል የመጀመሪያው ዙር የጉዞ መርሃ ግብር የተጀመረ ሲሆን በዚህም በመላው ዓለም የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው እየገቡ ይገኛሉ።
ስለሆነም ጥሪውን ተቀብላችሁ ከሀገራቹ ጋር ባህላዊ፣ ማህበራዊ እና ስነ-ልቦናዊ ቁርኝት ለመፍጠር በሚያስችለው አንዲሁም የህዝባችሁን ወግ፣ እሴት፣ ባህል፣ የዘመናት አኩሪ ታሪክ፣ አስደናቂ መልክዓ ምድር ገጽታ እና ውብ ተፈጥሮ በማወቅ በመላው ዓለም ለሚገኙ ህዝቦች ሁሉ ሀገራችሁን ለማስተዋወቅ በሚያስችላችሁ የዚህ ታላቅ ሀገራዊ ጥሪ አካል ለመሆን ከታች ባለው ሊንክ ወይም QR-Code ስካን በማድረግ እንድትመዘገቡ እያሳወቅን፤ ለተጨማሪ መረጃዎችን በስልክ: +44-773-738-6913 / +44-746-624-2530 ወይም በኢሜይል diaspora.officer@ethioembassy.org.uk መረጃ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
“Back To Your Origins!” a Call for 2nd Generation Diasporas! Register to the below Link or QR Code to be a part of this great national call.
Latest News
Browse allwe appreciate your help.