ኮቪድ-19፡ አስቸኳይ የወገን ለወገን ጥሪ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ለንደን
ለንደን፥ መጋቢት 27 ቀን 2012 ዓ.ም
በአገራችን ኢትዮጵያ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከተከሰተ ሳምንታት ተቆጥረዋል። ከጊዜ ወደጊዜ የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር እየጨመረ ይገኛል። እሁድ መጋቢት 27/2012 ዓ.ም ሁለት እንቁ ኢትዮጵያዊያን በዚህ አስከፊ በሽታ ውድ ህይዎታቸውን አጥተዋል። ከዚህ አንጻር የአገራችንን ሁኔታ ስናይ የጤናው ዘርፍ ባለበት የአቅም ውስንነት የሁሉም ዜጋ ድጋፍ ካልታከለበት በሽታው ከፍተኛ አደጋ ያስከትላል፡፡
በመሆኑም የቫረሱን ወረርሺኝ ለመከላከል መንግስት ካቋቋመው የብሄራዊ ሃብት ማሰባሰብ ኮሚቴ መመሪያ መሰረት በተጨማሪ ኤምባሲያችን በእንግሊዝ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እና ኢትዮጵያዊያን ወረርሺኙን ለመከላከል እገዛ የሚያደርጉበትን የሰው ሃብት፣ የገንዘብ እና ቁሳቁስ እርዳታ መንገዶችን ዘርግቷል።
ይህን አስከፊ ጊዜ ለማለፍ ለወገን ደራሽ ወገን መሆኑን አምነን ሕዝባችንን ከተጋርጠበት የገዳይ ቫይረስ ጭንቅና አደጋ በአስቸኳይ ደርሰን ለመታደግ የዳያስፖራው ሚና ከምንጊዜውም በላይ ወሳኝ ነው።
የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ለምትፈልጉ
ኤምባሲው ለዚሁ ጉዳይ ብሎ በከፈተው የባንክ አካውንት ማለትም
Account Name: Embassy of Ethiopia
Account No: 43178968
Sort Code: 30-65-41
እንድታስገቡ እንጠይቃለን፡፡
እንደአማራጭም https://bit.ly/COVID19xDonate የሚለውን ሊንክ በመጠቀም መላክ የምትችሉ መሆኑንና እንገልጻለን፡፡
የህክምና መሣሪያዎች /ቁሳቁስ መለገስ ለምትፈልጉ
ቁሳቁሶቹን በግልም ሆነ በጋራ በማሰባሰብ ሐሙስ በየሳምንቱ ከ11፡00 እስከ 13፡00 በኤምባሲው (17 ፕሪንስዝ ጌት፥ ለንደን SW7 1PZ) በመገኘት ማስረከብ የምትችሉ ሲሆን የሚፈለጉ ቁሳቁሶችን ዝርዝር ከዚህ በታች አባሪ መደረጉን እንገልጻለን፡፡
የሙያ ድጋፍ ማድረግ ለምትፈልጉ
በህክምናና ተያያዥ መስኮች እያገለገላችሁ የምትገኙ ወይም ስታገለግሉ የነበራችሁና የሙያ አገልግሎት መስጠት የምትፈልጉ የዳያስፖራ አባላትም በስልክ ቁጥሮች 07455 029 562 ወይም 07950 581 507 እንዲሁም በ business@ethioembassy.org.uk እንድታሳውቁን እንጠይቃለን፡፡
አስቸጋሪውን ጊዜ አሸንፈን እንሻገር
በዚህ ጥሪ ዙሪያ ለተጨማሪ መረጃ የዳያስፖራ ክፍላችንን ከስር በተዘርዘሩት ስልክ ቁጥሮች ማግኘት ይችላሉ፡ 07367 109 262 | 07939 956 086 | 07460 783 929.
የተፈለጉ የህክምና መሣሪያዎች ዝርዝር
- Mechanical ventilators (with all accessories included for adults) | x 1,000
- Mechanical ventilators (with all accessories included for children and newborns) | x 500
- Patient monitor (with all modules including NIBP and ECG) | x 1,500
- Electrical suction machine with 2 pumps | x 1,000
- Laryngoscope Macintosh, adult (with 3 blades, +2 spare bulbs and a carrying case) | x 2,000
- Oxygen face mask (adult size) | x 3,000
- Oxygen face mask (paediatric size) | x 500
- Oxymeter Pulse, fingertip model | x 5,000
- Oxymeter Pulse, fixed with all modules | x 500
- Respirator, mask, FFP2/N95, type IIR, s.u, unvalved, noseclip | x 150,000 boxes of 20
- Surgical face mask | 2,000,000 boxes of 50
- Thermometer, infrared, no contact, handheld | x 10,000
- Test kits
- COVID-19 E.gene for 100 tests | x 500 packs
- COVID-19 RDRP.gene for 100 tests | x 250 packs
- Invitrogen kit (Super Script III) for 100 tests | x 600 packs
- Extraction kit (Qiagen) | x 250 boxes of 250
- 5mg microcentrifuge tube (DnageRnase free) | x 600 bags of 1,500
- VTM (Viral Transport Medium) | x 1,000 boxes of 750
- Flocked swabs (polystrenetiped and plastic shaft) | x 1,200 boxes of 100
- Ultrasound machine, general purpose (chest and abdomen) | x 1,000
- Mobile x-ray | x 300
- ICU beds with mattress, side tables and overhead tables | x 1,500
- Oxygen concentrator | x 1,000
- CT Scan | x 4
- Ambulances (fully kitted with emergency set) | x 50
- Dialysis machine | x 15
- Consumables and reagents for Dialysis | x 35,000
-
Letter from the Ethiopian Ambassador
የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ለመከላከል በእንግሊዝ አገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ከክቡር አምባሳደር ፍስሃ ሻውል የተላከ ደብዳቤ
-
Together We Will Overcome!
Let us demonstrate as a nation and people that in the face of adversity, we rise to the challenge of confronting the Coronavirus, united by our responsibility to the home we call Ethiopia!
-
TOGETHER, WE CAN! Ethiopia leads calls for collective response to Coronavirus
Since the beginning of the Coronavirus crisis, Ethiopia has focused its strategy on the need for proactive interventions to curb the potential spread of the virus while putting in place the necessary infrastructure to ensure critical preparedness and capacity within the Health sector. In addition to the range of measures introduced since mid-January, the Government has maintained the importance of pursuing a joined-up approach with global solidarity at its core.
Latest News
Browse allwe appreciate your help.