ገበታ ለሀገር ዕውን ይሆን ዘንድ አሻራዎን ያኑሩ።
በታላቁ ብሪታኒያና ሰሜን አየርላንድ ለምትገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት
ለንደን
ለአገራችን የከተማ የቱሪዝም ዘርፍ ዕድገት ከፍተኛውን አስተዋጽኦ የሚጫወቱ የአዲስ አበባ ወንዞች ዳርቻ ልማት ፕሮጀክቶች አካል የሆኑት የታላቁ ቤተመንግስት አንድነት ፓርክ ፕሮጀክት፣ የእንጦጦ ፓርክ እና የኢትዮ ቻይና ትብብር ፓርክ በ ‘ገበታ ለሸገር’ የሃብት ማሰባሰብ ሂደት ከህዝብ እና ከልማት አጋሮች በተገኘ ሃብት በአጭር ጊዜ በስኬታማ ሁኔታ ተጠናቀው ለጎብኚዎች ክፍት መደረጋቸው ይታወሳል፡፡
እነዚህን ፕሮጀክቶች በተለያዩ የአገሪቱ አከባቢዎች በማስፋፋት በዘርፉ ሁለንተናዊ ለውጥ ለማምጣት በታቀደው መሰረት በመጀመሪያው ምዕራፍ በኮይሻ፣ በወንጪ እና በጎርጎራ የቱሪስት መዳረሻዎችን ለማልማት ለተጀመረው እንቅስቃሴ በተለያዩ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልድ ኢትዮጵውያን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች የፋይናንስ ድጋፍ እንዲያደርጉ መንግስት ጥሪ አቅርቧል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ በቀጣዮቹ ሳምንታት ውስጥ ለሚካሄደው የገቢ ማሰባሰብ ፕሮግራም መሠረት ኤምባሲያችን እ.ኤ.አ. ከኦክቶበር 28 ቀን እስከ ኖቬምበር 1 ቀን 2020 በማህበራዊ ሚዲያዎቹ የገቢ ማሰባሰብ ዘመቻ ያካሂዳል፡፡ በመሆኑም ሁላችሁም የዚሁ ዘመቻ አካል በመሆን የበኩላችሁን እንድትለግሱ መልካም ትብብራችሁን እየጠየቅን ቀጥሎ የተጠቀሰውን የባንክ አካውንት በመጠቀም ወይም በአካል በኤምባሲው በመገኘት የገንዘብ ድጋፉን ማድረግ የሚቻል መሆኑን በትህትና እንገልጻለን፡፡
Account Name: Embassy of Ethiopia,
Bank Name: Lloyds
Account No.: 43178968
Sort Code: 30-65-41
Reference: Gebeta
ከሠላምታ ጋር
ተፈሪ መለሰ ደስታ
አምባሳደር
***
-
በዩናይትድ ኪንግደምና ሰሜን አየርላንድ ለምትገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት
ለአገራችን የከተማ የቱሪዝም ዘርፍ ዕድገት ከፍተኛውን አስተዋጽኦ የሚጫወቱ የአዲስ አበባ ወንዞች ዳርቻ ልማትፕሮጀክቶች አካል የሆኑት የታላቁ ቤተመንግስት አንድነት ፓርክ ፕሮጀክት፣ የእንጦጦ ፓርክ እና የኢትዮ ቻይና ትብብርፓርክ በ’ገበታ ለሸገር’ የሃብት ማሰባሰብ ሂደት ከህዝብ እና ከልማት አጋሮች በተገኘ ሃብት በአጭር ጊዜ በስኬታማ ሁኔታ ተጠናቀው ለጎብኚዎች ክፍት መደረጋቸው ይታወሳል፡፡
Latest News
Browse allwe appreciate your help.