በዩናይትድ ኪንግደም ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም ኤርትራዊያን በጋራ የድጋፍ ሰልፍ አካሄዱ፡፡
ሚያዚያ 26 ቀን 2013 ዓ.ም
በዩናይትድ ኪንግደም በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት የተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ መላላትን ተከትሎ በለንደንና በስኮትላንድ በተካሄዱ የድጋፍ ሰልፍ በጠላቶቻችን ድብቅ ሴራ ምክንያት የብሄር ተኮር ጥቃት ሰለባ የሆኑ ወገኖቻችንን ለመዘከር፣ ብሄርና ማንነት ተኮር ጥቃትን መንግስት እንዲያስቆም እንዲሁም ጥፋተኞች ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል፡፡ ህዝባችንም ይህን ተገንዝቦ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል፡፡
የሰልፉ አስተባባሪዎች እንደገለፁት አንዳንድ ዓለም አቀፍ የሚዲያ ተቋማት እና መንግስታት እንዲሁም አንዳንድ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በተለይም በትግራይ ክልል ከተካሄደው የህግ ማስከበር እርምጃ ጋር ተያይዞ በተዛቡ መረጃዎች መነሻነት በኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ እንዲሁም በኤርትራ መንግስት ላይ እያደረጉት ያለውን አሉታዊ ዘመቻ በጽኑ አውግዘዋል፡፡
ሰልፈኞቹ መንግስት እየወሰደ ያለውን የህግ ማስከበር ሂደት አጠናክሮ እንዲቀጥል የጠየቁ ሲሆን፣ በውጭ ያሉ የጁንታው ቡድን አባላት ባለፉት ሦስት አስርተ ዓመታት ከኢትዮጵያ ህዝብ በዘረፉት ገንዘብ የሎቢ ቡድኖችን በከፍተኛ ገንዘብ በመቅጠር፣ ደጋፊዎቻቸውን እና ግብረ አበሮቻቸውን በማስተባበር የኢትዮጵያንና ኤርትራን ስም ለማጠልሸት እና የዲፕሎማሲ ጫና ለመፍጠር እያደረጉት ያለውን ጥረት በጽኑ ተቃውመዋል፡፡
የታላቁ የህዳሴ ግዳብ ድርድርን በተመለከተ ሱዳንና ግብፅ የሚያደርጉትን ኢፍትሃዊ ድርጊት በማውገዝ ለአፍሪካ ችግር አፍሪካዊ መፍትሄ በሚል ኢትዮጵያ የያዘችውን አቋም አጠናክራ እንድትቀጥል ጠይቀዋል፡፡ ሱዳን ዓለም አቀፍ ህግ በመጣስ የፈፀመችው ወረራ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ገልፀው፣ ቀጣዩ ምርጫ ሰላማዊ እና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ፣ ስልጣን የሚያዘው በምርጫ ብቻ መሆኑን አውቀው ማንኛውም አካል ከጥፋት እንዲቆጠብ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በተጨማሪም በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የተጀመረው ሰላማዊ ወዳጅነት ከምንጊዜውም በላይ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ያላቸውን ጽኑ ምኞት ገልፀው ድጋፍ እንደሚሰጡም አረጋግጠዋል፡፡
በድጋፍ ሰልፉ ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራዊያን በተጨማሪም የሁለቱም አገሮችና ወዳጆች ተገኝተው በሁለቱም አገሮች ላይ እየደረሰ ያለው ጫና መቆም እንዳለበትና ለዚህም ከሀገሮቹ ጐን እንደሚቆሙ ገልፀዋል፡፡
ሰልፈኞቹ በኢትዮጵያ ላይ እየተካሄደ ያለውን የተዛባ መረጃ መነሻ ያደረገ የስም ማጥፋት ዘመቻ በተመለከተ ለዩናይትድ ኪንግደም መንግስትና ለሚመለከታቸው ዓለም አቀፍ ተቋማት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በዩናይትድ ኪንግደም በDefend Ethiopia ግብረ ሃይል ከኢትዮጵያና ከኤርትራ ኮሚኒቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የድጋፍ ሰልፍ በአየር ላንድ ደብሊንና በሰሜን አየር ላንድ በኮቪድ ገደብ ምክንያት በዌቢናር በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ቀንና ሰዓት ተካሂዷል፡፡
Latest News
Browse allwe appreciate your help.