ከ 155 አመት በፊት ከመቅደላ ተዘርፎ የተወሰደው ጽላተ ቅድስት ድንግል ማሪያም ወ ቅዱስ ገብርኤል ታቦት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተመለሰ፡፡
ከ 155 አመት በፊት ከመቅደላ ተዘርፎ የተወሰደው ጽላተ ቅድስት ድንግል ማሪያም ወ ቅዱስ ገብርኤል ታቦት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተመለሰ፡፡
ዛሬ ለንደን በሚገኘው ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን በተካሄደ ስነስርአት ርክክቡ ተከናውኗል፡፡
በእለቱ በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ርእሰ አድባራት ለንደን ደብረጽዮን ቤተክርስቲያን የሃይማኖት አባቶች ፣ የብሄራዊ ቅርስ አስመላሽ ኮሚቴ ተወካይ ፣ ቅርሶቹን ለማሰመለስ የተባበሩ እና በዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ተገኝተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ልኡክን የመሩት መጋቢ ሀዲስ ቀሲስ አባተ ጎበና እንደተናገሩት ይህን ሃይማኖታዊና ታሪካዊ ፋይዳ ያለውን ታቦት ወደ ሀገሩ እንዲመለስ ከ ሁለት አመታት በፊት ጥረት መደረግ መጀመሩን አስታውሰው ፣ በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲን ጨምሮ ፣ የብሄራዊ ቅርስ አስመላሽና ይሀው ታቦት ወደሀገሩ እንዲመለስ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩትን የሼሄራዜድ በጎ አድራጎት መስራች እና ዶ/ር ጃኮብ ግኒሰኪን አመስግነዋል፡፡
ታቦቱ በተገቢው የሃይማኖት ስርአት ተይዞ ወደ ሀገሩ በቅርቡ እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡
የብሄራዊ ቅርስ አስመላሽ ኮሚቴ ተወካይ ፕሮፌሰር አሉላ ፓንክረስት በበኩላቸው በብሪታኒያ ሙዚየሞች ከ አስር በላይ የኢትዮጵያ ታቦቶች ያሉ በመሆናቸው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ፣ ኤምባሲው ፣ የጥናትና ምርምር ተቋማት ፣ የመንግስት ሃላፊዎችና የእምነቱ ተከታዮች በሙሉ የጀመሩትን የማስመለስ ጥረት አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል፡፡ታቦታቱ መንፈሳዊ ፋይዳቸው ለኢትዮጵያ ህዝብ እንጂ ለሙዚየም ባለመሆኑ ዛሬ በዚህ የርክክብ ስነስርአት ላይ የተገኛችሁ ሁሉ ይህን የማስመለስ ጥሪ እንድተቀላቀሉ ሲሉ ተናግረዋል፡።
ከታቦታቱ በተጨማሪ ሌሎች በርካታ ቅርሶች በግለሰቦችና በተለያዩ አካላት እጅ አሁንም ተይዘው ያሉ በመሆናቸው እሰኪመለሱ ግፊቱን አጠናክረን መቀጠል አለብን ብለዋል፡።
ለሁለት አመታት ታቦቱን ለማስመለስ ከኤምባሲው ፣ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንና እና ከብሄራዊ ቅርስ አስመላሽ ኮሚቴ ጋር በግል ሲሰሩና ሲያስተባብሩ የቆዩት ዶ/ር ጃኮብ ግኒስኪን በበኩላቸው በኢትዮጵያ ከልጅነታቸው ጀምሮ ማሳለፋቸውን ተናግረው ኢትዮጵያ በልጅነቴ ለዋለችልኝ ውለታ ከዚህም በላይ ለመመለስ እጥራለሁ ብለዋል፡።
ከ 2000 በላይ ምእመናን የተሳተፉበት የዛሬው ስነስርአት የኢትዮጵያ ወዳጅ የሆኑ የውጪ ሀገራት ዜጎችና የአካባቢው ባለስልጣናት ተገኝተዋል ፡
Latest News
Browse allwe appreciate your help.