የድጋፍ ጥሪ!
በዩናይትድ ኪንግደም ለምትገኙ ኢትጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን በያላችሁበት፣
ከሁለት አመታት በፊት በሁሉም የኢትዮጵያ ህዝቦች መስዋዕትነት የመጣውን ለውጥ ለመቀልበስ ሲታገል የቆየው የህወሀት ጁንታ ቡድን መግባባቶች በሰላማዊ መንገድ እንዲመጡ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ የነበረውን የአገሪቱን መንግስት ትዕግስት ከድክመት በመቁጠር ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ምሽት ጀምሮ ከ20 ዓመታት በላይ በክልሉ የሀገሩንና የህዝቡን ሰላም በመጠበቅ በኖረው ሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሠራዊታችን ላይ ባልተጠበቀ ሁኔታ በፈጸመው ኢሰብአዊ ድርጊት ጸረ ህዝብነቱን በማሳየቱ መንግስት በክልሉ የህግ ማስከበር እርምጃ መውሰዱ ይታወቃል።
ይህንን ያልተጠበቀና ሠራዊታችንን ለከፍተኛ መስዋዕትነት የዳረገ አስከፊ ድርጊት በመቃወም በዩናይትድ ኪንግደም የምትገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት መንግስት እየወሰደ ያለውን እርምጃ በመደገፍ ለመከላከያ ኃይላችን ድጋፋችሁን ለማድረግ ፍላጎታችሁን በገለጻችሁልን መሠረት ከኤምባሲው ጋር በጋራ የሚንቀሳቀስ ግብረ-ኃይል ተመስርቶ እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡
በመሆኑም ዳያስፖራው በሚኖርበት ኮንስቲትወንሲ ለፓርላማ አባላት አገራችን እየወሰደች ያለችውን ህግን የማስከበር እርምጃ ትክክለኛነት በማስረዳት እና በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚቀርቡ አፍራሽ አሉባልታዎችን በመመከት እያደረጋችሁ ያላችሁትን ጥረት እንድትቀጥሉ እየጠየቅን በዚህ በህወሀት ቀስቃሽነት በተጀመረው ጦርነት ለተጎዱ የሠራዊት አባላትና ቤተሰቦቻቸው ከዚህ ቀጥሎ በኤምባሲው በተከፈተ የባንክ አካወንት የቻላችሁትን የገንዘብ መጠን እንድትለግሱ በአክብሮት እየጠየቅን ተጨማሪ መረጃ ካስፈለጋችሁ በስልክ ቁጥሮች 073 6710 9262 / 079 3995 6086 / 075 7582 7053 መደወል ምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
Account Name: Embassy of Ethiopia
Bank Name: Lloyds Bank
Account Number: 43178968
Sort Code: 306541
Reference: National Army Veterans Support Fund (NAV Support Fund)
-
ከክቡር አምባሳደር ተፈሪ የተላለፈ የድጋፍ ጥሪ
Latest News
Browse allwe appreciate your help.