ኢትዮጵያ ያሏትን የኢንቨስትመንት አማራጮች፣ የካፒታል ገበያንና የሰነደ መዋእለ ነዋይ/ Securities Market/ እድሎችን ለንደን አየተካሄደ ባለው አለም አቀፍ የፋይናንስ ዘርፍ ጉባኤ ላይ አቀረበች፡፡

10 Oct 2023

“ኢንቨስት አፍሪካ 2023” በሚል ለንደን ላይ እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ የፋይናንስ ዘርፍ አመታዊ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ ከኢንቨስትመንት አማራጮች በተጨማሪ ለመጀመሪያ ጊዜ የካፒታል ገበያንና የሰነደ መዋእለ ነዋይ /Securities Market/ እድሎችን ለዩናይትድ ኪንግደም እና ከተለያዩ ሀገሮች ለመጡ በፋይንናስ እና በባንክ ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ ባለሃብቶች ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

10ኛ አመቱን በያዘውና ከመላው አለምና ከአፍሪካ በፋይናንስ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ባለሃብቶችን ያካተተው ኢንቨስት አፍሪካ 2023 ጉባኤ ላይ የገንዘብ ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰመሪታ ሰዋሰው የመሩት የልኡክ ቡድን፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ወ/ሮ ሌሊሴ ነሜ ፣ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ፣ የሰነደ መዋእለ ነዋይ እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ የስራ ሃላፊዎች እና በዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ተገኝተዋል፡፡

የገንዘብ ሚንሰቴር ሚንስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰመሪታ ሰዋሰው በጉባኤው ላይ እንደተናገሩት በኮቪድ ፣ በግጭት እና በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚከሰት ድርቅን ተቋቁሞ የኢትየጵያ ኢኮኖሚ ባለፉት ሶስት አመታት ከ 6.1 በመቶ በላይ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ አጠቃላይ አመታዊ ምርት ከ 126 ቢሊዮን ዶላር በላይ መድረሱን የተናገሩት ሚንስትር ዴኤታዋ የኢኮኖሚ እድገቱ የግሉን ዘርፍ በማካተት ይበልጥ ለማደግ የሚችልበት እድል ተከፍቷል ብለዋል፡፡

በተለይም ሁለተኛው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ዋነኛ ትኩረቱ የግሉን ዘርፍ በስፋት በማሳተፍ የተሻለ የኢኮኖሚ እድገትን ለማስዝገብ በቂ ዝግጅት መደረጉን አስረድተዋል፡፡

የፋይናንስ ዘርፉን ለሀገር ውስጥና ለውጪ ባለሃብቶች ክፍት ማድረግ ፣ የንግድና ኢንቨስትመንት ማነቆዎችን በመፍታት የተሳለጠ ምቹ ሁኔታን መፍጠር ፣ በግብርና ፣ በማንፋክቸሪነግ፣ በቱሪዝም ፣ በማእድን እና በአይሲቲ ዘርፍ ሰፊ እድሎች መመቻቸታቸውን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ያልነበሩ በአሁኑ ወቅት ግን የመንግስት የልማት ድርጅቶች ድርሻ 25 በመቶ ቀሪው ድርሻ ደግሞ በሀገር ውስጥና በውጪ ባለሃብቶች የሚሸፈንበት የፋይናንስ ኢንቨስትመንት ዘርፍ፣ የሰነደ መዋእለ ነዋይ /Securities Market/ በቅርቡ ይፋ መደረጉን አስታውሰው እነዚህ እድሎች ከፍተኛ የፋይናንስ ባለሃብቶችን በመሳብ ረገድ ሰፊ ሚና እንዳላቸው በመግለጽ ባለሃብቱ በዚህ ዘርፍ እንዲሰማራም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አያይዘውም የባንክ የህግና የቁጥጥር ስርአት ዝግጅቱ በመከናወኑ የባንክ ዘርፉን ለውጪ ባለሃብቶች ክፍት ለማድረግ ዝግጅት መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ወ/ሮ ሊሊሴ ነሜ በበኩላቸው በአሁኑ ወቅት የኢንዱስትሪ ፓርኮች የአንድ መስኮት አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን፣ ባለሃብቱ በማንፋክቸሪንግ ፣ በግብርና ፣ በፋርማሲዩቲካል ፣ በቱሪዝም ፣ በአይሲቲ ፣ በማእድን ዘርፎቸ ላይ ቢሰማራ ትርፋማ ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል፡፡

የኢንቨስትመንት ህጎችና መመሪያዎች አለም አቀፍ ደረጃቸውን ጠብቀው እንዲሰሩ ለማድረግ በየወቅቱ ማሻሻያ እየተደረገባቸው መሆኑን አስረድተው ኢትዮጵያ ካላት ምቹ የገበያ ፣ የጉልበት እና የጥሬ እቃ አቅርቦት አንጻር ተመራጭ እንደሆነች አስገንዝበዋል፡፡

በዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ መንግስት ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ተፈሪ መለሰ በሌላ በኩል እንደተናገሩት ኢትዮጵያ ለአለም አቀፍ ገበያ ስትራቴጂካዊ ቦታ ላይ እንደምትገኝ ገልጸው ፣ መላው አለምን ሊያገናኝ የሚችል የአየር መንገድ እና የካርጎ አገልግሎት ያላት ፣ በቂና የሰለጠነ ወጣት የሰው ሃይል የታደለች ፣ሸማች የሆነ ማህበረሰብ ያላት መሆኗ ተመራጭነቷን ያጎላዋል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በርካታ የኢኮኖሚ ፣ የፋይናንስ፣ የቴሌኮም፣ የህግና የተቋማት ሪፎርሞችን በማካሄዷ የዩናይትድ ኪንግደም ታላላቅ ኩባኒያዎች በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ላይ መሰማራት መቀጠላቸውን አስታውሰው ኤምባሲው ለባለሃብቶች የሚሰጠውን አገልግሎት ከምንጊዜውም በላይ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሰረድተዋል፡፡

የዩናይትድ ኪንግደም ኢንተርናሽናል ኢንቨስትመንት መስሪያ ቤት የስራ ሃላፊዎችም በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ላይ ለሚሰማሩ ባለሃብቶች አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን በጉባኤው ላይ ተናግረዋል፡፡

“ኢንቨስት አፍሪካ 2023” አለም አቀፍ ጉባኤ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒሰቴር ሚንስትር ዴኤታ የመሩት ልኡክ ዛሬን ጨምሮ ለሚቀጥሉት ሁለት ቀናት በአማራጮች ላይ ከባለሃብቶች ጋር የቡድንና የግል ውይይታቸውን ማድረጋቸውን ይቀጥላሉ፡፡

 

Latest News

Browse all
27 Feb 2024
Notice
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ኤምባሲ ለንደን የሚሸፍናቸው ሀገራት ነዋሪ ለሆናችሁ ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የቀረበ ታላቅ ሀገራዊ ጥሪ! ክቡር የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ሁለተኛው ትውልድ የኢትዮጵያ ዳያስፖራዎች በሦስት ዙር ወደ ሀገራቸው በመግባት ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ እና የባህል መሠረታቸውን እንዲያውቁ የቀረበውን ጥሪ በመቀበል የመጀመሪያው ዙር የጉዞ መርሃ ግብር የተጀመረ ሲሆን በዚህም በመላው ዓለም የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው…
11 Jan 2024
Back To Your Origins
UK pledges to increase dev’t aid to 200 mln Euros Ethiopia and United Kingdom (UK) have finalized to ink the Memorandum of Understanding (MoU) to scale up the diplomatic ties to strategic partnership level, said Ethiopian Ambassador to UK. In an exclusive interview with The Ethiopian Herald, Ethiopian Ambassador to the UK Teferi Melesse said that the activities are ongoing…
9 Jan 2024
Ethiopia-UK ties to enter ‘new era’
The Embassy of the Federal Democratic Republic of Ethiopia in London wishes you a joyful holiday season and prosperous New Year.
31 Dec 2023
Happy New Year 2024!
we extend our warmest invitation to you for the highly anticipated 1st Dire International Technology Expo 2024. As an influential figure in the technology sector, your presence at this groundbreaking event would be highly valued. Date: Jan 24 to Jan 28 / 2024 Venue: Dire Dawa Youth Sports Center Website: http://www.direinttechexpo.com The first Dire International Technology Expo 2024 is poised…
27 Dec 2023
Dire International Tech Expo
22 Dec 2023
Festive Message from Ambassador Teferi Melesse Desta
በለንደን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ኤምባሲ አስተባባሪነት ከዩናይትድ ኪንግደም ከሚገኙ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ጋር በመቀናጀት እ.ኤ.አ ከዲሴምበር 13-15/2023 ባዘጋጀው የልምድ ልውውጥ ፕሮግራም 11 አባላትን የያዘ የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የልዑካን ቡድን በለንደን ከተማ ከሚገኙ 3 የብሪታንያ የንግድ ምክር ቤቶች ጋር የልምድ ልውውጥና የትብብር ግንኙነት ውይይት አደረጉ፡፡ ሶስቱ የንግድ ም/ቤቶች የብሪቲሽ ንግድ ም/ቤት፤ የብርቲሽ-ኢትዮጵያ ንግድ ም/ቤትና የለንደን ንግድ ም/ቤት ናቸው። በሶስቱም መድረኮች…
15 Dec 2023
የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የልዑካን ቡድን የለንደን ቆይታ
7 Dec 2023
Notice
The main office of the Global Black History, Heritage, and Education Centre (GBHHEC) will be officially established in Addis Ababa on Friday, December 08, 2023. Lead by Ambassador Teferi Melesse, Ethiopian Ambassador to the United Kingdom and North Ireland, a delegation of founding board members of the Global Black History, Heritage, and Education Centre (GBHHEC) landed in Addis Ababa. Director…
6 Dec 2023
Ethiopia will remain the center of important historical, cultural, and diplomatic initiatives.
በኤፕሪል 1973 ወደ ዩናይትድ ኪንግደም በረራውን ቦይንግ 720-ቢ አውሮፕላን በመጠቀም በሳምንት ለሁለት ቀናት የጀመረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ወቅት አጅግ ዘመናዊ የሆኑ ኤርባስ 350 እና ቢ787 ድሪምላይነር አውሮፕላኖችን በመጠቀም በሳምንት ለአስር ጊዜያት በቀጥታ በረራ እያካሄደ መሆኑ ተመልክቷል፡፡ በዚህም ከአስር ሺህ በላይ መንገደኞችን ወደ 60 አለም አቀፍ መዳረሻዎች እያጓጓዘ መሆኑን በዩናይትድ ኪንግደም እና አየርላንድ የአየር መንገዱ ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡ በለንደን ሂትሮ እና…
23 Nov 2023
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም የሚያደርገውን በረራ በሳምንት ወደ አስር ጊዜያት ማሳደጉን አስታወቀ፡፡
On the sidelines of the Global Food Security Summit the Ethiopian Ambassador to UK H.E. Ambassador Teferi Melesse Desta met with British International Investment and AgDevCo to discuss potential investment and collaboration in Ethiopia. The Ambassador commended the work done with EthioChicken and explained the robust potential Ethiopia has attract even more investment.
21 Nov 2023
Ambassador Teferi met with BII and AgDevCo
We are excited to announce the inaugural flight of Ethiopian Airlines from Addis Ababa to Gatwick Airport landed earlier today! This new route marks an important milestone in Ethiopian Airlines commitment to providing convenient and seamless travel options for passengers between the UK and Ethiopia. We look forward to welcoming you on board as we connect the vibrant city of…
21 Nov 2023
Ethiopian Airlines Started new route to London Gatwick Airport.