ኢትዮጵያ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ 2023 የሚካሄደውን አለም አቀፍ የሎርድ ክሪኬት ውድድር ፕሮግራም እንድታስጀምር ተመረጠች፡፡
በአለማችን ዝነኛ በሆነውና በቢሊዮን የሚቆጠር ተከታታይ ባለው ሎርድ የክሪኬት ክለብ ተገኝተው የ2023 አለም አቀፍ የክሪኬት ውድድር ዲጂታል ኳስ ኢትዮጵያን በመወከል መርቀው ያስጀመሩት በዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ተፈሪ መለሰ ኢትዮጵያ ጥንታዊ የስልጣኔ ሀገር፣ የበርካታ ባህላዊና ዘመናዊ ሰፖርት ባለቤት መሆኗን ተናግረዋል፡፡
አክለውም በቅኝ ግዛት ያልተገዛች ብቸኛዋ ሀገር፣ለተቀረው አለም ትሩፋት የሚሆን የዳበረ ታሪክና ባህል ያላት ሀገር መሆኗንም አስረድተዋል፡፡
በአለማችን የረጅም ርቀት ሩጫ አትሌቶች ምንጭና የርቀቱ ባለድሎች ሀገር እንደሆነች የተናገሩት አምባሳደር ተፈሪ ይህ በአለም አደባባይ በተደጋጋሚ የተመሰከረለት ነው ብለዋል፡፡
የአፍሪካ ህብረት መቀመጫና የአለማችን ሶስተኛዋ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ መሰባሰቢያ የሆነቸው ኢትዮጵያ በዚህ ዝነኛ በሆነው ሎርድ የክሪኬት ክለብ የ2023 ውድድርን ለማስጀመርና የክሪኬት ዲጂታል ኳስ ለመመረቅ በመመረጧ ደስታ ይሰማናል ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ መሰል የሆኑ የራስዋ ባህላዊና ዘመናዊ ሰፖርቶች ባለቤት መሆንዋን የገለጹት አምባሳደር ተፈሪ የክሪኬት ስፖርት በኢትዮጵያ እንዲስፋፋና ተደራሽ እንዲሆን ለማድረግ ከታዋቂውና ከ200 አመታት በላይ ታሪክ ካለው ማሊበን የክሪኬት ክለብ ጋር በቅርበት ተባብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
አክለውም ኢትዮጰያ ለንግድ፣ ለኢንቨስትመንት እና ለቱሪዝም ምቹ ሁኔታዎች ያሏት ሀገር መሆኗን ያስተወቁት አምባሳደር ተፈሪ ለአለም ገበያ ቅርብ የሆነች ፣ በቂ እና የሰለጠነ ወጣት ያለባት ሀገር መሆኗን ተናግረዋል፡።
የስታር አሊያንስ አባል የሆነና በሰባ ሶስት ሀገሮች አንድ መቶ ዘጠኝ መዳረሻዎች ያሉት የኢትዮጰያ አየር መንገድ ከ አንድ መቶ በላይ እጅግ ዘመናዊ የሆኑ የመንገደኛ እና የካርጎ አውሮፕላኖች ባለቤት መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡
በተያያዘ ዜናም ይህን የዲጂታል ኳስ ምረቃ ካመቻቸው የ ኤአይኤክስ /AIX –HOLDING/ ሆልዲንግ ጋር በመተባበር በቀጣዩ ወር በአቅም ግንባታ፣ በቴክኖሎጂና በእውቀት ሽግግር በዩናይትድ ኪንግደምና በኢትዮጰያ መካከል ያለው ግንኙነት ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በኢትዮጵያ ኤምባሲ በሚካሄደው “Invest Africa worldwide 2022 “ መድረክ ላይ የክለቡ አባላትና ሌሎች ባለሃብቶች እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
Latest News
Browse allwe appreciate your help.