የብሪታኒያ መንግስት ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጠል ተጠየቀ

31 Mar 2022
የዩናይትድ ኪንግደም መንግስት ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን የልማት ትብብርና ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጠል የብሪትሽ ፓርላማ ጥምረት ቡድን በመንግስታቸው ላይ ግፊት እንዲያድርጉ ተጠየቀ፡፡
በዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ተፈሪ መለሰ በፓርላማ ተገኝተው ለብሪትሽ ፓርላማ ጥምረት ቡድን አባላት በሰጡት ወቅታዊ ማብራሪያ የዩናይትድ ኪንግደም መንግስት ለኢትዮጵያ የሚያደርገው የልማት ድጋፍ ወደቀደመው መጠኑ እንዲመለስ የፓርላማ አባላቱ በመንግስታቸው ላይ ግፊት እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡
የዩናይትድ ኪንግደም መንግስት ከአውሮፓ መውጣቱን ተከትሎ በካሄደው የውጪና የመከላከያ ፖሊሲ ክለሳ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቅድሚያ ትኩረት ከተሰጣቸው ሀገሮች ዋናዋ እንደነበረች ያስታወሱት አምባሳደር ተፈሪ የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱም በተገባው ቃል መሰረት እንዲቀጥል ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
አምባሳደር ተፈሪ አያይዘውም የአለም አየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ኢትዮጵያ በፖሊሲና በእቅድ የአረንጓዴ አሻራ ልማትን ቀርጻ ከራሷ በማለፍ ለጎረቤት ሀገሮች እና ለአንዳንድ የአፍሪካ ሀገሮች ድጋፍ እያደረገች መሆኗን ገልጸዋል፡፡ያደጉ ሀገሮች የአለም አየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የገቡትን የአንድ መቶ ቢሊዮን ዶላር በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት የሚደረግ ድጋፍ በተገባው ቃል መሰረት እንዲፈጸም የዩናይትድ ኪንግደም መንግስት የጀመረውን ግፊት አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የኢትዮጵያን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ በማስመልከት አምባሳደር ተፈሪ እንዳሉት ኢትዮጵያ ሰላምን በተመለከተ ቁርጠኛ አቋም እንዳላት ለብሪትሽ ፓርላማ አባላት አስረድተዋል፡። በሀገር ውስጥ ያለውን ስር የሰደደ ችግር በመግባባት ለመፍታት በመላው ኢትዮጵያ በብሄራዊ ደረጃ ሁሉን አቀፍና አሳታፊ የውይይት መድረክ በቅርቡ መካሄድ እንደሚጀምር ተናግረዋል፡፡
መንግስት ለዚህ መግባባት እንዲያመች በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ተከስቶ የነበረው ግጭት በተመለከተ ወታደራዊ ዘመቻው መቆሙን ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መነሳቱን ፣ ቁልፍ የቀድሞው ፖለቲካ አመራሮች በምህረት እንዲፈቱ መደረጉን እና ለሰብአዊ ድጋፍ የሚያስችሉ እርምጃዎችን መወሰዱን አመልክተዋል፡፡
የብሪትሽ ፓርላማ አባላት በበኩላቸው ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እየወሰደች ያለውን እርምጃ እንደሚከታተሉ እና አድናቆታቸውን እንደሚገልጹ ተናግረው ፣ ያደጉ ሀገሮች የገቡትን ቃል እንዲፈጽሙ በዩናይትድ ኪንግደም መንግስት በኩሉ ግፊቱ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
ዩናይትድ ኪንግደም ለኢትዮጵያ የምትሰጠው ድጋፍ ከኮቪድ ተጽእኖ እና በአለም አቀፉ ኢኮኖሚ ቀውስ ምክንያት እንደቀነሰ እንደሚረዱ ያመለከቱት የፓርላማ አባላቱ በኢትዮጵያ ላይ ያሳደረውን ተጽእኖ በመጠየቅ ለመንግስታቸው እንደሚያቀርቡ አስረድተዋል፡፡
አምባሳደር ተፈሪ በሰጡት ማብራሪያ የልማት ድጋፍና ትብብሩ በትምህርት ፣ በጤና ፣ በእናቶችና ሕጻናት እንዲሁም በማህበራዊ ዘርፎች መሆኑን አስታውሰው በርካታ ውጤታማ ተግባሮች መከናወናቸውን አመልክተዋል፣ ሆኖም ግን የድጋፍ መጠኑ በመቀነሱ
በእቅድ የተያዙ የማህበራዊ አገልግሎቶች አፈጻጸምን እንዳጓተተ ተናግረዋል፡፡

Latest News

Browse all
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ኤምባሲ ለንደን የሚሸፍናቸው ሀገራት ነዋሪ ለሆናችሁ ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የቀረበ ታላቅ ሀገራዊ ጥሪ! ክቡር የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ሁለተኛው ትውልድ የኢትዮጵያ ዳያስፖራዎች በሦስት ዙር ወደ ሀገራቸው በመግባት ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ እና የባህል መሠረታቸውን እንዲያውቁ የቀረበውን ጥሪ በመቀበል የመጀመሪያው ዙር የጉዞ መርሃ ግብር የተጀመረ ሲሆን በዚህም በመላው ዓለም የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው…
11 Jan 2024
Back To Your Origins
UK pledges to increase dev’t aid to 200 mln Euros Ethiopia and United Kingdom (UK) have finalized to ink the Memorandum of Understanding (MoU) to scale up the diplomatic ties to strategic partnership level, said Ethiopian Ambassador to UK. In an exclusive interview with The Ethiopian Herald, Ethiopian Ambassador to the UK Teferi Melesse said that the activities are ongoing…
9 Jan 2024
Ethiopia-UK ties to enter ‘new era’
The Embassy of the Federal Democratic Republic of Ethiopia in London wishes you a joyful holiday season and prosperous New Year.
31 Dec 2023
Happy New Year 2024!
we extend our warmest invitation to you for the highly anticipated 1st Dire International Technology Expo 2024. As an influential figure in the technology sector, your presence at this groundbreaking event would be highly valued. Date: Jan 24 to Jan 28 / 2024 Venue: Dire Dawa Youth Sports Center Website: http://www.direinttechexpo.com The first Dire International Technology Expo 2024 is poised…
27 Dec 2023
Dire International Tech Expo
22 Dec 2023
Festive Message from Ambassador Teferi Melesse Desta
በለንደን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ኤምባሲ አስተባባሪነት ከዩናይትድ ኪንግደም ከሚገኙ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ጋር በመቀናጀት እ.ኤ.አ ከዲሴምበር 13-15/2023 ባዘጋጀው የልምድ ልውውጥ ፕሮግራም 11 አባላትን የያዘ የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የልዑካን ቡድን በለንደን ከተማ ከሚገኙ 3 የብሪታንያ የንግድ ምክር ቤቶች ጋር የልምድ ልውውጥና የትብብር ግንኙነት ውይይት አደረጉ፡፡ ሶስቱ የንግድ ም/ቤቶች የብሪቲሽ ንግድ ም/ቤት፤ የብርቲሽ-ኢትዮጵያ ንግድ ም/ቤትና የለንደን ንግድ ም/ቤት ናቸው። በሶስቱም መድረኮች…
15 Dec 2023
የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የልዑካን ቡድን የለንደን ቆይታ
7 Dec 2023
Notice
The main office of the Global Black History, Heritage, and Education Centre (GBHHEC) will be officially established in Addis Ababa on Friday, December 08, 2023. Lead by Ambassador Teferi Melesse, Ethiopian Ambassador to the United Kingdom and North Ireland, a delegation of founding board members of the Global Black History, Heritage, and Education Centre (GBHHEC) landed in Addis Ababa. Director…
6 Dec 2023
Ethiopia will remain the center of important historical, cultural, and diplomatic initiatives.
በኤፕሪል 1973 ወደ ዩናይትድ ኪንግደም በረራውን ቦይንግ 720-ቢ አውሮፕላን በመጠቀም በሳምንት ለሁለት ቀናት የጀመረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ወቅት አጅግ ዘመናዊ የሆኑ ኤርባስ 350 እና ቢ787 ድሪምላይነር አውሮፕላኖችን በመጠቀም በሳምንት ለአስር ጊዜያት በቀጥታ በረራ እያካሄደ መሆኑ ተመልክቷል፡፡ በዚህም ከአስር ሺህ በላይ መንገደኞችን ወደ 60 አለም አቀፍ መዳረሻዎች እያጓጓዘ መሆኑን በዩናይትድ ኪንግደም እና አየርላንድ የአየር መንገዱ ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡ በለንደን ሂትሮ እና…
23 Nov 2023
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም የሚያደርገውን በረራ በሳምንት ወደ አስር ጊዜያት ማሳደጉን አስታወቀ፡፡
On the sidelines of the Global Food Security Summit the Ethiopian Ambassador to UK H.E. Ambassador Teferi Melesse Desta met with British International Investment and AgDevCo to discuss potential investment and collaboration in Ethiopia. The Ambassador commended the work done with EthioChicken and explained the robust potential Ethiopia has attract even more investment.
21 Nov 2023
Ambassador Teferi met with BII and AgDevCo
We are excited to announce the inaugural flight of Ethiopian Airlines from Addis Ababa to Gatwick Airport landed earlier today! This new route marks an important milestone in Ethiopian Airlines commitment to providing convenient and seamless travel options for passengers between the UK and Ethiopia. We look forward to welcoming you on board as we connect the vibrant city of…
21 Nov 2023
Ethiopian Airlines Started new route to London Gatwick Airport.
“We have no intention of threatening the sovereignty of any nation but we would like a rules based access to the Red Sea. Our request is to initiate discussions towards sustainable solutions.” “What we seek to accomplish as a nation requires clarity of thought. It also requires hard work on a daily basis. Although there are many issues contributing to…
14 Nov 2023
PM Abiy Ahmed Responds to MP’s